Sunday, March 9, 2014
የኢትዮጵያን ለኢትዮጵያ ወይም የወያኔን ለወያኔ
ሚሊዮን ሊማ ከኖርዌይ
በአንድ ወቅትአንድ ዘጋቢ የኢትዮጵያን ባንዲራ በሚመለከት ተዘዋውሮ ካናገራቸው የመዲናይቱ ነዋሪዎች አንዱ፥ “እኛ አገራችንን የምንወደው ወያኔዎች ስለነገሩን አይደለም። እሱማ ባንዲራችንን ባጥላሉበት ዘመንም አገራችንን እንወድ ነበር፤ አሁንም እንወዳለን፤ ወደፊትም እንወዳለን። ይህ በደማችን ውስጥ ያለና መቼም ቢሆን ከልባችን ሊወገድ የማይችል ነገር ነው፤” ብለው እንደነበር አስታውሳለው ።

ሰንደቅ ዓላማችን እንዳገራችን እራሷ ባለታሪክ ናት። ሰንደቅ ዓላማችን፣ እነሱ እንዳሏት “ጨርቅ” ብቻ ሳትሆን ስንት ደም የፈሰሰባት ወድቃ የተነሳች ልዩ የታሪካችን መዘክርና የማንነታችን ማብሰሪያ ሰንደቅ ናት።
አቶ ኦባንግ ሜቶ እና አቶ አብዱላሂ ሁሴን በኖርዌይ ኦስሎ ከኢትዮጵያውያንና ከኖርዌጅያን ባለስልጣናት ጋር ተወያዩ
አቶ ኦባንግ ሜቶ የአዲሲትዋ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ፓሬዝዳንትና አቶ አብዱላሂ ሁሴን የኦጋዴን ክልል ፕሬዝዳንት አማካሪ የነበሩና በክልሉ የሚደረገውን የህዝብ ጭቆና፥ እንግልት፥ ግድያ የሚያሳዪ ወደ መቶ ሰአታት የሚደርሱ የቪዲዮ ማስረጃዎችን ይዘው በመሰደድ ለአለም ህዝብ እያጋለጡ ያሉና በአሁኑ ሰአት በስዊድን ሃገር የፖለቲካ ጥገኝነት አጊንተው የሚኖሩ ሲሆን ከማርች 6 እስከ ማርች 7 ,2014 በነበራቸው የኖርዌይ ቆይታቸው ከተለያዩ የኖርዌይ ባለስልጣናት ጋር በሃገራችን ውስጥ ስለሚደረገው የሰብአዊ መብት ረገጣ በማስረጃ በተደገፈ ውይይት ያደረጉ ሲሆን፥ በመቀጠልም በነበራቸው ቆይታ ስፖንሰር አድርገው ባመጧቸው Solveig Syversen በተባሉ አክቲቪስትና እንዲሁም Frontline Club Oslo በተሰኘ ድርጅት በተዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ በመቶዎች የሚቆጠሩ ኖርዌጂያንና ኢትዮጵያውያን Filmenshus በተባለ ቦታ ተገኝተው በኢትዮጵያ ውስጥ እየተደረገ ያለውን የሰብአዊ መብት ረገጣ በማስረጃ በተደገፈ ለህዝብ ያቀረቡ ሲሆን ከታዳሚውም በተነሱ የተለያዩ ጥያቄዎች ላይ ውይይት ያደረጉ ሲሆን፥ ማርች 7/2014 የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ የድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ አጋጣሚውን በመጠቀም በጠራው አስቸኴይ ስብሰባ አቶ ኦባን ሜቶ እና አቶ አብዱላሂ ሁሴን ከኢትዮጵያውያኑ ጋር ሰፋ ያለ ውይይት ያረጉ ሲሆን በቀጣይም በሃገራችን እየተደረገ ያለውን የሰብአዊ መብት ጥሰት፥ ግድያ፥ እስራት ለማስቆም ምን መሰራት አለበት
Subscribe to:
Posts (Atom)