Friday, October 11, 2013

የተሞሉትን የሚተነፍሱ ጠቅላይ ሚኒሰትር – JONAS TAMERU ( OSLO NORWAY )


pm-hailemariam
ለሁለት  አስርተ አመታት በኢትዮጲያና  በህዝቦቿ ላይ ነግሶ በማን አለብኝነት አድራጊ ፈጣሪ ሆኖ በሁሉም ያገሪቱ አቅጣጫዎች ሰላማዊውን ህዝብ ለሞትና ለስደት እንዲሁም ለእስር ሲዳርግ የነበረው አምባገነኑ የህውሃት ዘረኛ ቡድን የመለስ ዜናዊ  ሞት ተከትሎ በይስሙላ ምርጫ ያስቀመጠው አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ የዚሁ ዘረኛ ቡድን ደቀ መዝሙር ሆኖ በነሱ በመቃኘት ተፈጥሮአዊ ባህሬያቸውን ወርሶ አሁንም በሃገራችን  ስርዓቱ ካለው እኩይ ተፈጥሯዊ  ባህሪ አንፃር የናፈቅነውንና የተመኘነውን ነፃነትም ሆነ ለውጥ ሳይመጣ እነሆ ሌሎች ንፁሃን ሲገደሉና ሲሰደዱ እንዲሁም ሲታሰሩ አየን ሰማን፡፡

ለብዙሃን ዜጎች ህይወት መጥፋት፣ መሰደድና በየእስር ቤቱ መታጎር ተጠያቂ የሆነው አምባገነኑ የወያኔ ቡድን እንዲሁም ስርዓቱ  በተለይ ሃገር ሲያፈርሱ፣ ሲመዘብሩና ደሃውን የህብረተሰብ ክፍል ሲየፈናቅሉና በችጋር ሲቆሉ የነበሩት የህወሃት መስራቾች በዘፈቀደ ባገኙት አጋጣሚ እዚህ ምስኪን ህዝብ ላይ አፋቸውን ማላቀቃቸውን መዘባበታቸው የተለመደ ቢሆንም   የወያኔ ጠ/ሚንስትር አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ በተለያየ አጋጣሚ በስርዓቱ መገናኛ ቡዙሃን ቀርበው የሚሰጡት አስተያየትም ሆነ የሚናገሩት እጅግ የወረደና ስነምግባር የሌለው ዲስኩር ሰውየው በራሳቸው ሳይሆን ስርዓቱ እንደፈለገ እንደሚዘውራቸው ፍንትው አርጎ የሚያሳይ ነው፡፡