Friday, January 18, 2013

የጥፋት ራእይ፤ የክህደት ሌጋሲ

 
ራእይም ይባል ሌጋሲ፤ህልምም ይባል ምኞት አንድ ነገር እውነት ነው። ሰውየው፤ከተጀመረ ጀምሮ በሰላም ኑሮ እንቅልፍ አግኝቶ ስለማያውቅ ህልም አለመ፤ራእይም ነበረው፤አስቦና መዝኖ ሠራ ለማለት አይቻልም። ከፊቱ ነገ አልነበረችም። ሊባል የሚቻለው፤ የነበረው የጥፋት፤ የማፍረስ፤ የመበተን፤ የክህደት ቅዠት ብቻ ነው።
 
የዛፉ ምንነት በሚያፈራው ፍሬ ይመዘናልና፤ የተዋቸውን እናስቀጥላለን ከሚባለው ራእይ ባዶ ኳኳታና ጩኸት ማካከል ጥቂቶችን እንመልከት። ውሸት ሲደጋገም እውነት ይመስላል እንዲሉ፤ያልነበረውን እንደነበረ፤ ባዶውን እንዳለ፤ የማይሆነውን እንደሚሆን ሲሰበክና ሲቅራራ ሲወሸከት ሕዝብ እንደታዘበ፤ ታሪክም እንደመዘገበና የፈጠጠው እውንታ የሚታይ መሆኑን መካድ አይቻልም። ሚዛኑ፤የሕዝቡ የእለት እለት ኑሮ፤ያለው ነጻነትና መብት፤ስነልቡናው፤የዓለምአቀፍ ሕብረተሰቡ የሚወተውተው ምን እደሆነ ማየት ነው።
 
ዓይናችሁን ጨፍሉ ላሞኛችሁ፤እንደሰጎን ራስን አፈር ውስጥ ቀብሮ አልታይም-የብልጣብልጥ ሞኝነት ሲዘበት ሁለት አስርተ አመታት እንደለፉ፤ በእነዚህ ወርቃማ አመታት መልካም አስተዳደር፤ ቅን አመለካከትን ጥረት ታክሎበት አገር ትመጥቅ ነበር ማለት ምኞት ብቻ ቢሆንል፤ በእድገቷ ከሌሎቹ ቀርቶ ከአአህጉር እህት አገሮች ጋር በተስተካከለች ነበር፤ ምን ያህል ብዙ በተሰራ ነበር ያሰኛል። በእርግጥም ብዙ ሕይወት ተገብሯል፤ ሕዝብ ተጎሳቁሏል፤ መብት አልባ ሖኗል፤ ታፍኗል፤ ታስሯል፤ ተሰዷል፤ አገር ተበትናለች፤ ንብረት ባክኗል፤ በአገር በሕዝብ ላይ ከመቸውም የበለጠ አደጋ አንዣቧል።
 
እውነቱ ሌላ፤የሚወራው ሌላ። ብዙ ጊዜ በማደናቆር፤በመዋሸት፤በማሳሳት፤በተንኮልና ሸፍጥ አልፏል።
 
ህልምና ቅዠት፤ እውነትና ውሸት፤ማታለል፤መደለልና እውነተኛ ሕዝባዊ አረማማድን ሌለውም ሌላውም ሕዝቡ በሚገባ ለይቶ ስለሚያውቅ፤ነገ እንደታሪክ እንደሚወራ ማዘንጋት አያሻም። ትላንት ዛሬ ነበረች፤ ዘሬም ነገ ትሆናለች፤ ባጭሩ እንደማንኛውም ስርአት፤ ይኸም ስርአት ይሻግታል፤ይበሰብሳል ያልፋል። እውነታው ግን ለትውልድ ፈጥጦ ይቀራል።
 

 ከእንግዲህ የሚሞኝ ከተገኘ በራሱ ፈረደ። ወደድንም ጠላንም፤የመዋሸት፤የማታለል፤የክህደት፤የጥፋት ጊዜ፤አብቅቷል። ሁሉም እርምጃውን ጠብቆ፤ጊዜውን ቆጥሮ ይመጣል። የተሰጋጀም ተዘጋጀ፤ የባከነም በከነ፤ጊዜው ሲደርስ እንደበሰበሰም ሆነ እንደ እንተዘመመ እንዳልነበረ ሲሆን፤ዞር ብሎ ትላንትን በመልከምም በሌላም መቃኘት አይቀርም። በተለያየ መልኩ፤ብዙ ዝምታ መስማማት ቢመስልም፤ከምዙ ዝምታ በሗል አበይት ክስተቶች ይኖራል። የሕዝብም ዝምታ ከዚሁ አይለይም። ዝም አለ ከተባለ ማለት ነው።
 
ብዙ ሳንርቅ፡ይህ ራእይ እየተባ ሲነገርለትና እንቀጥለው የሚባለው ምኑ ነው? ዲሞክራሲ ቢባል ዲሞከራሲ የለም፤ ነፃነት ቢባል፤ ነጻነት የለም፤መብት ቢባል መብት የለም፤እድገት ቢባል እድገት የለም-የሕዝቡ ኖሮ ምስክር ነውና፤እንደተባለውም “ምንም የለም”፤ሁሉም የለም። ታድያ እንቀጥል የሚባለው ምኑን ነው? በነበረው በአስ ጉልበት እንቀጥል ከሆነ፤የሆነው ለመቀጠል አያበቃም፤ቢመኙትም ከሕዝብ ፍላጎት ውጪ ነው። ፊት በሐይል በጡንቻ ነበር፤የማያስኬድ መንገድም አይደለም። ሃይልም ቢባል፤ የሃይል ምንጭና ሃይል የት እንዳለ ማስተዋል ያስልጋል።
 
ነገርን ቢደጋግሙት መሰለቻቸት ነው። እስኪ አበይት ነጥቦችን እንወርውር።
 
1. ያገር ክህደት የአገር መሸጥ ሌጋሲ፤
 
አገርን ወደብ አልባ እንዳላደረገ፤ያዋሳኝ ለም መሪትን ለጎራባች አገር አሳልፎ እንዳልሰጠ፤የአገሪቱን ለም መሬት በማን አለብኝነትና ቅን አስተሳሰብ በጎደለው የግድ የለሽ ውሎች፤ድሀ ገበሬን ከመኖሪያው ፈንቅሎ በርካሽ መቸብቸብ እድገትንም ልማትንም እደማያመጠ፤ ጅማሬውም ፍጻሜውም ግልጽ የሆነው፤ የክህደት፤የቅዠት ጉዞ ሊዘነጋ አይገባም። ባለ ራእዩ ያተረፈን የተዘጋች፤ለአምሳና ከዚህም በላይ ዓመታት የተሸጠች አገር ነች።
 
2. የታሪክ ክህደትና ማጉደፍ ሌጋሲ፤
 
ጠለቅ ያለ ዝርዝር ከመስጠት አንጥቦ ለማለፍ፤የዘመናትን ታሪክ ሽሮ ሚሊኒየም እንዳላከበር፤የጀግኖች ልጆችዋን ታሪግ በባዶ እብሪትና ትምክህት እንዳላንኳሰሰ፤ እንዳላጎደፈ፤እንቀጥል የሚባለው የጥፋት መንገድ ይህ ነው-ታሪክን መካድ መሻር ማንኳሰስ።
 
3. የአገር ብተና ሌጋሲ፤
 
አገርን በዘር፤በቋንቓ ሽንሽኖ ለትውልድ የማይሽር የጥፋት መረብ የዘረጋ ያስተዳደር ስልተ፤ፈጠነብ ዘገየ ጊዜውን ጠብቆ የሚፈነዳ የጥፋት ቀመር ለመሆሉ በየጊዜው የታየ አሁንም እንደሰደድ እሳት በየአራት ማእዘን እየጤሰ ያለ፤የሚአስቀጥል ራእይ ወይስ የጥፋት ቅዠት?
 
4. የዘረፋ ሌጋሲ፤
 
በእድገት ጭራ፤በዘረፋ ከአለም ቀደምት፤ ከድሃ አፍ ነጥቆ በውጭ ባንኮች ሀብትን ማድለብ፤ በሺ ብር ደሞዝ የሚሊዮን ብር ህንዳ መገንባት፤ ከመንግስት ተበድሮ ሰይከፍሉ መበልጸግ፤ ከመንግስት ካዝና ወርቅ ብር በሚሊዮን የሙቆጠር መዝረፍ፤ መጋዘኖችን ወዘተ ባዶ ማድረግ፤ ያገሪቱን ኢኮኖሚ መቆጣጠር፤ የዜጎችን እጅ ማሰር፤ ስንቱ ይነገራል። ይህ ነው እንግዲህ የሚያስቀጥል ራእይ። እራስን መታዘብ ቢያቅት፤ ሌሎች እንደሚታዘቡ መገመት ምንኛ ብልህነት ነው። የለመደበትን እጅ ለመሰብሰብ ይበጅ ነበር። በቀደምት ስርአቶች ያልታየ። የህን በዚህ እንተወው።
 
5. የአፈና ሌጋሲ፤
 
ሕዝቡ፤የሕዝቡ ልጆች፤ ወጣቱ፤ምሁራኑ አፋቸው እንዳይናገር፤ ዓይናቸው እናዳያይ፤ብእራቸው እንዳይፅፍ፤ እዳይሰበሰቡ፤እንዳይደራጁ፤ለአገር እንዳይመክሩ፤ ለመብት ለነጻነታቸው እንዳይቆሙ፤ይህንንም ካደረጉ፤ በህግ ከለላና ህግ ከሚፈቅድላቸው ውጪ የግፍ ግፍ ሲዘንብባቸው ለመኖሩ በየፈርጁ የተመዘገበ፤በቂ ማስረጃና ሕያው ዋቢ ያለው የሚያስጠይቅ እየቀጠለ ያለ ሂደት መሆኑ ባጽንኦ መጤን አለበት። በዚህ መስክ የጥፋቱ ራእይ እንደቀጠለ መሆኑ አይካድም።
 
6. የጥፍጠፋ (Cloning) ሌጋሲ፤
 
የፖለቲካ ድርጅቶችን፤የሲቪክ ማህበራትን፤ የሀይማኖት ድርጅቶችን በየፈርጁ እያሰላ በመጠፍጠፍ፤ሁሉንም በመልኩ ቀርጾ ሕዝብን በገዛ አገሩ፤በቤቱ፤በእምነቱና በባህሉ ባእድ ያደረገ የጥፋት መንገድ ከእርሱ ለእነነርሱ ራእይ እውነታው ግን የቅዠት መንገድ ነው።
 
7. የድምጽ መስረቅ ሌጋሲ፤
 
መዝግቦ ለማለፍ፤ለማስታወስ ካልሆነ በቀር፤ አይን ያወጣ የሕዝብ ድምጽ በቀትር ጠራራ ጸሀይ ሰለባ ሲካሄድ፤ደግሞ ተደጋግሞ ይባስ ብሉ በ99.6% ነጥብ አሸንፈናል ለማለት የበቃ፤እዚህ ላይ እየተሰረቀ ያለው የሕዝብ ድምጽ ሕዝብ ከነሕይወቱ መሆኑን ነው። ይህ ለእነርሱ የዲሞከራሲ ሌጋሲ ለእኛ ግን የሕዝብ ድምጽ በጠራራ ጸሀይ ሕዝብን ከነነፍሱ መዝረፍ ነው። ይህችም ፊደል በምትነጥብበት ወቅት እንኳ የሕዝም ድምጽ ለማፈን ለመዝረፍ ደባው እየቀጠለ ነው። ወይ ራእይ!
 
8. የአምባገነንንት ሌጋሲ፤
 
ከላይ በታያያዘ መልኩ፤ለሓያ አመታት፤አንድ ጊዜ ባለ ሙሉ ባለስልጣን ፕሬዘዳንት፤ በሚቀጥለው ጊዜ ባለ ሙኑ ስልጣን ጠቅናይ ሚኒስቴር፤ ሌለው እነዚህን የስልጣን እርከኖች ሲጨብጥ ባዶ እያደረገ የዘለቀ የሃያ አመት መሰሪ ላጠፋው ጥፋት ለፍርድ ሳይቀርብ ለማለፉ ለእነርሱ የመልካም አስተዳደር ራእይ፤ሌጋሲ ለታሪክ ግን አምባከነን የመሆኑን እውነታ ማሰቀመጥ ያስፍልጋል።
 
9. የውሸት የሀሰት የትእቢት ሌጋሲ፤
 
የሆነውን አልሆነም፤ያልሆነውን እንደሆኗል፤የነበረውን አልነበረም ያልነበረውን ነበር እይተባለ አይንን በጨው ያጠበ ነጭ ውሸት፤ፈሩን የሳተ የፐሮፐጋንዳ ዘመቻ ሲደለቅ አመታት ለማለፋቸው ሕዝቡ ከእነርሱ አንደበት የሚወጣው እንደማይጥመውና ጆሮውን እንደነፈጋቸው፤በልቡ ከእነርሱ እንደራቀ፤እንደካዳቸው፤ጊዜንና አጋጣሚን እየጠበቀ አንዳላ ከነርሱው አንደበት “የተቀመጥንብተ ወንበር የዛፍ ላይ እንቅልፍ” ሆነብን እስከሚሉ፤በእውነትም ራእይ ሳይሆን ቅዠት ላይ እንደጣላቸው፤ይህንንም ቅዘት ራእይ ብለው ሊመክሩ እደተነሱ አራሳቸውም አልዘነጉትም። ራእይና ቅዠት አንደ እይደሉም። ሲያንቀላፉ ከሳፉም መውደቅ። የውሸትና የትእቢተኝነት ሌጋሲ።
 
10. የዘር ማጥፋት ሌጋሲ፤
 
በአገሪቱ ለብዙ ጊዜ ባራቱም ማእዘናት፤ዘርን መሰረተ ያደረገ የጥፋት ዘመቻ የንጹሀን ደም በከንቱ ለጥቅም ለስልጣን ሲባል ሲፈስና ሲማገድ እንደነበር፤አሁንም በቅርቡ ድሀ ተገን የሌላቸው ዜጎች እየተማገዱ በየጥሻው እየተጣሉ እንዳሉ መዘንጋት አያሰፈልግም። የጥፋት ዘመቻው ለእነርሱ የሚቀጥል ራአይና ሌጋሲ ለዜጎች የሞት ሽረት ጉዳይ ሆኗል። ገበያ ባልወጣሽ የሚሉሽን ባልሰማሽ አሉ።
11. የትውልድ አፍራሽ፤የተበከለ ባህል ሌጋሲ፤
 
የዜሬው ትውልድ እዳለ ሆኖ የነገው ትውልድ የትምህርት፤የጤና፤የማህመራዊ ፤የእምለት ባጠቃላይ ተስፋው ጨልሞ፤ለአደገኛ ባህሎች፤ልምዶች ታጋልጦ፤በስራአጥነት ተጠምዶ በያለብት ወድቆ የወገን ያለህ፤የአገር ያለህ ሲል እንደሚታይ ሊደበቅ በማይይቻል መልኩ በያደባባዩ ተሰጥቶ ያለ እውለታ ነው። ካሁን በፊት የልነበሩ ያለተለመዱ የጥፋት ልምዶች፤ትውልድ አምካኝ ሂደቶች እንዳሽን እየፈሉ ለመሆናቸው እራሳቸው የማይክዱት፤ባለ ሌጋሲ የሚባለው መሰሪ ላገር ለትውልድ ያተረፈው የጥፋት ቅዠት ነው።
 
12. የአገርን ጥቅም አሳልፎ የመስጠት ሌጋሲ፤
 
ሞኝ እነደላኩት ነው ይሏል። እንዳዘዙት፤እንደሰደዱት፤የአገርን ሳይሆን የባእድን ጥቅም በማስቀደም፤ሲፈልግም በሪሞት ኮንትሮል የምንንቀሳቀስ የበናና ሪፑብሊክ አይደለንም እያለ፤ሲያሻው ሳንቲም ከእነርሱ አላገኘንም እያለ ሲሸመጥጥ በያለበት ወጣቱን እያስማገደ፤የወገንን ጉዳት ደብቆ፤ምስኪኑን በረሀ በልቶት እነደቀረ ለእነርሱ የሚቀጥል ሌጋሲ ለወገን ለአገር ግን የክህደት፤የአገርን ጥቅም መሸት ወንጀል ነው። ይህ ነው እንግዲህ እንቀጥል የሚባለው ቅዠት።
 
13. ኪራይ ሰብሳሚነትና የሞኖፖሊ ሌጋሲ፤
 
አገሪቱን በየፈርጁ -የፖለቲካ የኢኮኖሚ፤የመከላከያ፤የሰኩሪቲ፤የሲቪክና የእምንተ አውታሮችን ተቆጣጥሮ፤እኒህን በመመርኮስ ሊቃና ወደማይችል የኪራይ ሰብሳም የጥቅም ማጋበሻ ስርአት መስርቶ እንቀጥል፤በዚሁ ይቀጥል የሚለው ከንቱ ምኞት የሗላ ሗላ በእራስ ላይ መፍረድ መሆኑ ማታውቅ ይኖርበታል። ሕዝብ ኪራይ ሰብሳቢ ቢሉት፤ የቤት ኪራይ የመሬት ኪራይ እንዲመስለው በሚያሰለች መልኩ ሲደጋጋም ቢሰማም፤ሚስጥሩ የመንግስት ስልጣንን በመጠወም ሀብ ከማግበስብስ፤ሌላው ስርቶ እንዳይጠቀም በስልጣን ሀይል ማገድ መሆኑ ሊታወቅ ይገባል። ስርአቱ የተመቻቸው ለምዝበራ-ሊቃናም የማይችል የጥፋት ራእይ-ቅዠት ነው።
 
 
14. የተዋረደ ኢኮኖሚ ሌጋሲ፤
 
በዚሁ ሂደት በእድገት ጭራ፤በዝርፊያ ቀዳሜ፤ባሳቻ ቀመር አንደኝነትን የያዘ ስርአት ለመሆኑ ብዙ መዘርዘር አያስፈልግም። ስንቱ ብለቶ ጠጥቶ የድራል፤የስንቱ መሰረታዊ ፍላጎቶች ተሟሉ፤አምራች ዜጋና ምርት የትና የት ናቸው፤ማን ምንነ ይቆጣጠራል፤ማን አደገ ተመነደገ፤ማንስ ድሃ ሆነ ተብሎ ቢጠየቅ መልሱ እዛው ፈላ እዛው ሞላ፤ እኔን ከደላኝ እድገት ይህች ናት ነው። እነርሱ ሲበሉ ሕዝብ የጠገበ ይመስል፤ብዙሀኑ እንደትላንቱ መከራቸውን እየገፉ ነው።
 
ታዲያ፤ላገር ለወገን መልካም እንደሰራ፤እያፈነ፤እያደናቆረ በሕይወቱ በቁሙ በደነዘ ካራ አንገቱን ሲገዘግዘው የነበረን፤ይተደራረበ ወንጀለኛ፤መልከም እንዳደረገ፤የሕዝብ ገዳይ፤የአገር ሻጭ፤የታሪክ ነቀዝ፤በተንኮል መበመሰሪነት የተጠመደን መጥፎ ከሀዲ፤መዘዙ ለትውልድ የሚዘልቅን የጥፋት መልእክተኛ፤ባለራእይ፤ባለሌጋሲ አድርጎ በጥፋት መስመሩ እንቀጥል ማልት፤በቀላሉ፤ሰው የለንም፤ እስካሁን እርሱ ነበረ አበቃልን፤የተንኮል ምንጫችን ደረቀጭ መንገዳችንን እንፈልግ፤ ከእንግዲህ የሚሰማን የለም ቢሉ ይቀላል። በሌላ በኩል ደግሞ አስበው መሥራት አለመቻልን በራሰ የመተማመን ጉድለትን ያሳያል፤ዱሮስ።
 
 
የለፈውም አለፈ-ግልግል፤አዲሱም ታየ-ለውጥ የለውም። ሁሉም ለትምህርት ይሁን። መንገድ መንገድ መንገድ።
ቋያ ቋያ ጢሱ እየጢያጤሰብሽ፤
ዳሩ መሃል ሆኖ እሳቱ ሳይበላሽ፤
አገሬ ተነሼ ሌላም መንገድ የለሽ።
ቸር ያሰንብትልን!

No comments:

Post a Comment